አሜሪካ በሱዳን ላይ ጥላው የቆየችው የኢኮኖሚ ማዕቀብን ልታነሳ ነው

አሜሪካ በሱዳን ላይ ጥላው የቆየችውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ሙሉ በሙሉ ልታነሳ እንደምትችል የተባባሩት  መንግሥታት ድርጅት  አስታወቀ ፡፡

ድርጅቱ እንዳለው ማዕቀቡ መነሳቱ  በሃገሪቱ የሚከናወኑ  የሰብዓዊ ድጋፎች እንዲጠናከሩ ይረዳል፡፡

የአሜሪካና የሱዳን ግንኙነት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ወደ መልካም ግንኙነት እየተመለሰ ነው፡፡

አሜሪካ በሱዳን ላይ እኤአ በ1997 ነበር የኢኮኖሚ ማዕቀብ የጣለችው፡፡ ማዕቀቡን ለመጣል ያነሳሳት ደግሞ ሱዳን አሸባሪዎችን ትደግፋለች የሚለው የመጀመሪያው ነው፡፡ በሀገሪቱ የዜጎች የሰብዓዊ መብት አያያዝም ሌላኛው የማዕቀቡ መጣል ምክንያት ነበረ፡፡

ይህን ማዕቀብ ተከትሎ ግን ሱዳን በኢኮኖሚዋ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ላይ ደርሷል የሀገሪቱ የሲቪል አቬሽን ኢንዱስትሪም የማዕቀቡ ገፈት ቀማሽ ነው፡፡

የሱዳን የፋይናንስ ሚኒስትሩ ባድር አል ዲን ማህሙድም አሜሪካ ጥላው የቆየችውን ማዕቀብ በቅርብ ቀን እንደምታነሳ ነው ያላቸውን ተስፋ የሚገልፁት፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሜሪካ በሱዳን ላይ ላለፉት ሃያ ዓመታት ጥላው የቆየችውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ልታነሳ እንደምትችል ነው ያስታወቀው፡፡

ድርጅቱ እንዳለው አሜሪካ በሱዳን ጥላው የቆየችውን ማዕቀብ በማንሳቷ በሀገሪቱ ለሚደረገው የሰብዓዊ መብት እርዳታዎች እንዲጠናከሩም ይረዳል፡፡

በሱዳን የሚገኘው የተባበሩት መንግስት ድርጅት ቡድን ባለፉት ስድስት ወራት በሀገሪቱ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፉ ለማሻሻል የተፈረመው ስምምነት ለውጥ ማምጣቱን አስታውቋል፡፡

በሱዳን መንግስትና በሰብዓዊ ድጋፍ ሰጭ አካላት መካከል ያለው መተባበርም ለውጤቱ መገኘት የራሱን አስተዋፅኦ አበርክቷል ብሏል ድርጅቱ፡፡

አሁን በሱዳን የሚታየውን የሰብዓዊ መብት መሻሻል የበለጠ ለማጠናከር አሜሪካ ጥላው የቆየችውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ በቅርብ ጊዜያት ሙሉ በሙሉ ልታነሳው እንደምትችል ያለውን ተስፋም ድርጅቱ ገልጧል፡፡

የሰብዓዊ መብት ድጋፍ ሰጭዎች ቁጥር አሁን በሱዳን ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎታቸውን  እያሳዩ ነው የሀገሪቱ መንግስትም ቢሆን ለዚህ ተግባር ያለውን ቁርጠኝነት እየገለፀ ነው፡፡

የአሜሪካ መንግስት እስከ እሮብ በሀገሪቱ ጥሎት የቆየውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ያነሳል ወይም ሙሉ በሙሉ ማዕቀቡን የሚያነሳበትን ቀን ያሳቀውቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የዘገበው የቻይናው ዓለም አቀፍ የቴሌቭዥን ኔትወርክ ነው፡፡