ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእስያ ቆይታቸው የ300 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት አደረጉ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእሲያ ቆይታቸው ለአሜሪካ የ300 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ስምምነት መፈራረማቸው ተገለጸ ፡፡

የአላስካው የነዳጅ ፕሮጀክት ደግሞ ከስምምነቶቹ ግዙፉ ሲባል፣ የነዳጅ ፕሮጀክቶቹን ጨምሮ ሌሎች የብዙ ቢሊየን ዶላር ስምምነቶች ተግባራዊ ስለ መሆናቸው ግን ጥርጣሬዎች ተበራክተዋል፡፡

12 ቀናትን በፈጀዉ ረጂሙ የኤዥያ 5 ሀገራት ጉብኝት ላይ የከረሙት የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ዋሽንግተን ተመልሰዋል፡፡

ትራምፕ በጃፓን፣ ኮሪያ፣ ቻይና፣ ቬይትናም እና ኢንዶኔዥያ ቆይታቸው በተደጋጋሚ አጥብቀው የተናገሩት ከእሲያ ሀገራት ጋር ያላቸውን የንግድ ሚዛን ስለማስጠበቅ ነው፡፡

 ሰውየው በጉብኝታቸዉ አሜሪካ ከሀገራቱ ጋር በምትፈጥረዉ የንግድ ሽርክና 300ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚያስገኝላትን የንግድ ስምምነቶችን ፈጥረው ተመልሰዋል ተብሏል፡፡ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘውን የንግድ ስምምነት ደግሞ ያደረጉት ከቻይና ጋር ነው፡፡

"በንግዱ ረገድ አሁን ላቅ ያለዉን እርምጃ ተጉዘናል፡፡ ከቻይና ጋር ብቻ 250 ቢሊየን ዶላር ሊያስገኝልን የሚችለውን የንግድ ስምምነት ከመፈራረማችን ውጪም ከጉብኝታችን ብዙ ብዙ አትርፈናል," ትራምፕ በኢንዶኔዥያ ቆይታቸው በማኒላ ከተናገሩት ነው፡፡

ነገር ግን በሰውየዉ ጉብኝት ብዙም ግልፅ ያልሆኑ ነጥቦች ተነስተዋል፡፡ ስምምነቶቹ ካሁን በፊት የነበሩትን ስምምነቶች ስለማካተት አለማካተቱ የታወቀ ነገር የለም፡፡ ስምምነቶቹ በከፊል አስቀድመውም እንደመዘገባቸው ትራምፕ በጉዞአቸው ያሉትን ያህል ያተረፉ አይመስልም ይላል የቢቢሲ ዘገባ፡፡

ከኃይል ስምምነታቸው ደግሞ በትልቅነቱ የሚነሳው የቻይናው የኃይል ኢንቨስትመንት ኮርፖሬሽን 83ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ መስማማቱ ነዉ፡፡

በስምምነቱ መሰረት ቻይና በቨርጂኒያ ግዛት በምታደርገዉ የ2 አስርት አመታት ቆይታ የኬሚካል ምርት ፕሮጀክቷን ታከናዉናለች፡፡

ይህ ስምምነት እስካሁን በትልቅነቱ ከሚነሳዉ የአላስካዉ ጋዞሊን ልማት ኮርፖሬሽን ከቻይና መንግስት የነዳጅ ኩባንያ ሲኖፔክ፣ የቻይና ባንክ እና የቻይና ኢንቨስትመንት ኮርፖሬሽን ጋር ካደረገዉ የ43 ቢሊየን ዶላር ስምምነትም በእጥፍ የላቀ ነዉ፡፡

ነገር ግን አሜሪካ ሰሞኑን በእሲያ ሀገራት ስታደርግ የነበረዉ የተፈጥሮ ጋዝ ስምምነቶች ያልፀና ተብሏል፡፡ ሁለት የአሜሪካ የነዳጅ ኩባኒያዎች ኤ.ኢ.ኤስ እና አላስካ ጋስሊን ልማት ኮርፖሬሽን ከቬይትናሙ ፔትሮ ቬይትናም ጋስ ጋር ያደረገዉ የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ሌላዉ በኃይል ልማት ላይ የተደረሰ ስምምነት ነው፡፡

አሜሪካና ጃፓንም በኃይል አቅርቦት ላይ በደረሱበት የጋራ መግባባት ኋይት ሃዉስ በደቡብ ምስራቅ ኢሲያ፣ ደቡብ ኢሲያ እና ከሰሀራ በታች የአፍሪካ ሀገራት ተደራሽነቱ ከፍ ያለ የነዳጅ አቅርቦት ላይ ለመሳተፍ ውጥን ስለመያዟ ያስረዳል፡፡

ትራምፕ በጉዞአቸው ሀገራቸው ከቻይና ጋር ያደረገቻቸዉ ስምምነቶች በልዩ ትኩረት ሊያዙ የሚገባ ነው ተብለዋል፡፡ በሲንጋፖር  የነዳጅ አገልግሎት ጄ ቲ ዲ ዉስጥ በዳይሬክተርነት የሚያገለግሉት ጆን ዲሪስኮል እንዳሉት ቻይና በነዳጅ ኩባኒያዎቿ የምታሳርፈዉን ተፅዕኖ ለአመታት ማስቀጠል ተፈልጋለች፡፡

የቻይና የነዳጅ ኩባንያዎች በተለያዩ የዓለም ሀገራት ከአፍሪካ እስከ እሲያ፣ ከላቲን አሜሪካ እስከ ካናዳ በሰፊዉ የነዳጅ ምርመራ ላይ ሲሳተፍ ይህ የዓለሙም 2ኛው ግዙፍ ምጣኔ ሃብት የአሜሪካን ደጅ ግን ረግጦም አያዉቅም፡፡

የአለማችን ግዙፍ የነዳጅ ክምችት ያላት እና በተፈጥሮ ጋዝ ምርት የምትመራዉ አሜሪካ ላይ በዚህ ወቅት የተያዘው አቅጣጫ ደግሞ ለቻይናዎቹ ኩባንያዎች እንደ አዲስ ያልተሄደበት አቅጣጫ ተይዟል፡፡

በሙርዶክ ዩኒቨርሲቲ የእሲያ ጥናት ማዕከል ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ጀፍሪ ዊልሰን ለቢቢሲ እነደተናገሩት የሲኖ ፔክ ስምምነት የሚና ከሆነ የቻይናን ተፅዕኖ በአሜሪካ ጎልቶ እናገኘዋለን ብሏል፡፡

በ2005 የቻይና የነዳጅ ኩባንያዎች የአሜሪካ የነዳጅ ኩባኒያ የሆነዉን ዩኖካልን ለመግዛት ጨረታ ሲገባ በፖሊቲካ እይታ ቢቻ ከዉድድሩ መሰረዛቸዉን አስታዉሰዋል ደክተሩ፡፡

ከዚያን ጊዜ በኋላ ሲኖፔክን ጨምሮ አንድም የቻይና የነዳጅ ኩባንያ በአሜሪካ የነዳጅ ኩባንያ ውስጥ ለመግባት ጥረት ሲያደርግ አልተመለከትንም፡፡ 

የቨርጂኒያው የ83ነጥብ7 ቢሊየን ዶላር ስምምነት ግን አሜሪካ የከሰል ኢንዱስቲሪዋን ከማነቃቃትም በላይ በትራምፕ አዲስ የፖሊቲካ እና ኢኮኖሚ መንገድ ስለመቀየሷ የሚያስተላልፈው መልክት አለው ይላሉ ዶክተር ጀፈሪ ዊልስን፡፡

ቻይና እጅግ የገዘፈ የራሷ የሆነ የነዳጅ ክምችት ላይ ተቀምጣ ነዳጁን ለማውጣት በሚያስከፍለው ከፍተኛ ዋጋ ሚክንያት እጇን አጣጥፋ ለመቀመጥ መገደዷን ያስረዳሉ ዶክተር ጀፈሪ ዊልሰን፡፡

ሲኖፔክ ከአሜሪካዉ የነዳጅ ማዉጫ ካምፕ ልምድም ጭምር ቀስሞ የሚመለስበት ጥቅሙ ቀላል የማይሆነው በዚሁ ሚክንያት መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ስምምነቶቹ ተግባራዊ ስለመሆናቸው ግን ጥርጣሬዎች ተበራክቷል፡፡ ምንም እንኳ የነጩ ቤት ኃላፊዎች ፕሮጀክቱ ለ12 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጥር ነው ቢባልም የአላስካ ነዋሪዎች ከነበረዉ ልምድ እምብዛም ለአከባቢው ነዋሪዎች የስራ ዕድሉ ተጠቃሚ ሲሆኑ አለመስተዋሉ ለፕሮጀክቱ እንቅፋት እነዳይሆን ተሰግቷል፡፡

ትሮጀክቱን ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ ዋጋ የሚጠይቅ መሆኑ ደግሞ ሌላዉ ስጋት ነዉ፡፡ ( ምንጭ: የቢቢሲ እና ሲ ኤን ኤን)