አሜሪካ ከፍተኛ የጦር መርከቦቿን ወደ ሰሜን ኮሪያ አቅራቢያ መላኳ ተሰማ

አሜሪካ ወደ ሰሜን  ኮሪያ አቅራቢያ ከፍተኛ የጦር መርከቦችን መላኳ ተገለጸ ፡፡

የጦር መርከቦቹ ከጫኑት አውዳሚ የጦር መሳሪዎች በተጨማሪ 14ሺህ ወታደሮች መኖራቸው ተገልጿል፡፡ ይህም አሜሪካ ጃፓንን ከመሳሰሉት አጋሮቿ ጋር በቀጣናው የጦር ልምምድ ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት የሚያግዝ ነው ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል የሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ዮንግ ኡን በበኩላቸው የዘመኑ ከባድ የተባበለትን የባላስቲክ ሚሳኤል ተሸካሚ ሰርጓጅ እየገነባች መሆኑን አስታዋቃለች፡፡

አሜሪካ ከሰሜን ኮሪያ ጋር የገባችበት መቋጫ አልባው እሠጣ ገባ በአካባቢው ውጥረቱ ነግሶ እንዲቀጥል አድርጓል፡፡

ፕሪዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሳምንት በዘለቀው የእስያ ጉብኝት የሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ዋና አጀንዳቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ወደ አገራቸው ከመመለሳቸው ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ወታደር እና አውዳሚ የጦር መሳሪያ የጫኑ መርከቦችን ወደ ቀጣናው መላካቸው ጉዳዩን አስገራሚ አድርጎታል፡፡

የወጡት ዘገባዎች እንደሚያለክቱት አሜሪካ ለሰሜን ኮሪያ መጀመሪያ ማስጠንቀቂያ የሚሆን ዝግጅት ለማድረግ ከ14ሺህ በላይ ወታደሮችን ወደ ቀጣናው ልካለች፡፡

ይህን ዘመቻ በመጀመሪያ የተቀላቀለችው ደግሞ የአሜሪካ ወዳኝ ነኝ ባይዋ ጃፓን ነች፡፡ ሁለቱ ሀገራት በጋራ በኦኪናዋ ውቅያኖስ ላይ ልምምድ ለማድረግ ወደ ስፍራው ተንቀሳቅሰዋል፡፡ በሚቀጥሉት አስር ቀናት ውስጥም ወደ ቦታው ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አሜሪካ ወደ ሥፍራው የላከቻቸው የጦር መርከብ፣የጦር ወታደሮች እና ዘመናዊ የጦር አውሮፕላኖች የሰሜን ኮሪያን የባላስቲክ ሚሳኤል ማውደም የሚችሉ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ አሜሪካ ይህን መሰል መሳሪያና የጦር ኃይል ስትልክ እአአ ከ2007 በኋላ የመጀሪያው ነው ተብሏል፡፡

የአሜሪካ የጦር መርከቦችን ወደ ቀጠናው መላክ የጃፓን እና የአሜሪካን መቀራረብ ቢያሳይም ከፒዮንግያንግ ጋር የገባችበትን ፍጥጫ የሚያባብስ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

በውቅያኖሱ ላይ ከሚደረገው ልምምድ በተጨማሪ አሜሪካና ጃፓን የመጨረሻ የጦር ቴክኖሎጂያቸውን የሚያሳዩበትም ነው ተብሏል፡፡ ልምዱም በዋናነት የሚሳኤል ማምከን፣ የአየር ላይ እና የውሃ አካል ላይ ልምምዶች ትኩረት አድርጓል፡፡

የአሜሪካ ጦር ቃል ኣቀባይ እንደተናገሩት ልምምዱ ከአስር ቀናት በላይ ይወስዳል፡፡ በሰሜን ኮሪያ ላይ ጫና ለመፍጠር እና ሰሜን ኮሪያ ለምታደርጋቸው የማስፈራራት ስራ አሜሪካ ቁጭ ብላ መጠባበቅ ብቻ ሳይሆን ለፒዮንግያንግ የጦር መሳሪዎቿ ወዳሉብት ተንቀሳቅሶ አስፈላጊዉን ምላሽ ሊሰጥ የሚችል መሳሪያ እንዳለም ለማሳየት ነው ብለዋል፡፡

አሜሪካ ወደ ጃፓኑ የባህር ከላከችው ግዙፍ የጦር መርከብ በተጨማሪ በደቡባዊው ውቅያኖስ ላይም መጠነኛ ልምምዶችን እየደረገች እንደምትገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡  በዚህም ቀጣና ላይ ከተወሰኑ የጀፓን እና የደቡብ ኮሪያ የጦር ኃይሎች ጋር ተቀላቅለዋል፡፡