ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰሜን ኮሪያ ለአሸባሪዎች ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጹ

ሰሜን ኮሪያ ለአሸባሪዎች ድጋፍ  የምታደርግ አገር መሆኗን  የአሜሪካ  ፕሬዚደንት ዶናልድ  ትራምፕ  አስታወቁ ።

ፕሬዝዳንቱ ሀገሪቷ ከድርጊቷ እንድትቆጠብ የዓለም አቀፉ ማህበረስብ ጫና እንዲያደርግ ያሳሳቡ ሲሆን አሜሪካ በሰሜን ኮሪያ ባላት አቋም ከተወሰኑ ሀገራት ድጋፍ እያገኘች ነው፡፡ 

አሜሪካ ሰሜን ኮሪያን ከሸባሪዎች መዝግብ ላይ ስሟን መስፈሯን አስታወቀች፡፡ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በነጩ ቤተመንግስት ለካቢኒያቸው ንግግር ባደረጉበት ወቅት የሰሜን ኮሪያ የኒውክለር ፕሮግራምን ክፉኛ በመንቀፍ  በአሸባሪነት ድርጊት ወንጅለዋታል፡፡፡

ፕሬዚዳንቱ በካቢኒያቸው ጉባኤ ላይ ይፋ ባደረጉት አቋማቸው ሰሜን ኮሪያ በተለይ በቅርቡ ባደረገቻቸው የኒውክለር ቦምብ እና የሚሳኤል ሙከራ መነሻ በማድረግ  ከመዝገቡ ስሟን ማስፈራቸውን ያስታወቁት፡፡   

ሰሜን ኮሪያ በዚህም ድርጊቷ በፕሬዝዳንቱ አመኔታ በድርጊታቸው ከሽብርተኝነት መዝገብ ላይ ከሰፈሩ ኢራን ፣ ሱዳን እና ሶሪያ ተርታ አስቀምጧታል፡፡

ዘ ጋርዲያን በዘገባው እንደመለከተው ሰሜን ኮሪያ ከዚህ ቀደም በዚህ መዝገብ ላይ በሽበርተኝነት ከተወነጀሉ ሀገራት ተርታ ሥፍራ የነበረ ሲሆን እንደጎርጎሮሲያዊያኑ የዘመን ቀመር በ2008 ከዝርዝሩ ውስጥ ወጥታ ነበር፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው በዘመነ ጆርጅ ቡሽ መንግስት በተደረገው ድርድር ነው፡፡   

በመስከረም ወር የትራምፕ አስተዳደር የሰሜን ኮሪያ አደገኛውን የሃይድሮጂን ሙከራ ማድረጓን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት የነዳጅ እገዳን እንዲጥልባት እቅዱን አቅርቦ ነበር፤ ከዚህም በተጨማሪ የኪም ጆንግ ኡን አስተዳደር ሰከን እንዲል ጫና እንዲያሳድር የሚወተውት ደብዳቤ አስገብቷል፡፡     

አሁን ትራምፕ ሀገሪቱ ከድርጊቷ እየተቆጠበች አይደለም በማለት በሽብርተኝነት መዝገብ ዳግመኛ ከማስፈር በተጨማሪ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ጠንካራ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ሊጥሉ ተዘጋጅተዋል፡፡

የአሜሪካ ሰሜን ኮሪያን በሽብርተኝነት መዝገብ ላይ ማስፈር ሁለቱ ሀገራት እንዲነጋገሩ በር ሊከፍት ይችላል ተስፋ አለው፡፡

አሁን አሜሪካ በሰሜን ኮሪያ ላይ ባላት አቋም ከሌሎች የአለም ሀገራት የምትፈልገው ድጋፍ በለስ እየቀናት ይመስላል፡፡

ቻይና ፒዮንያንግን ለማስከን አሜሪካ በምታደርገው ጥረት ከጎኗ መሆኗን ገልፃለች፡፡ በተለይ ሁለቱ ሀገራት ባላቸው ልዩነት ላይ እንዲመክሩበት እየወተወተች ነው፡፡ ኪም ጆንግ ኡን ግን በበኩላቸው አሁንም ሌላ ተከታታይ የኒውክለር እና የሚሳኤል ሙከራ ለማድረግ እየተዘጋጁ መሆኑ ተውቋል፡፡( ምንጭ: የዘጋርዲያንና ቢቢሲ)