እስራኤል በደማስቆ አቅራቢያ የሚሳኤል ጥቃት ማድረሷ ተገለጸ

በሶሪያ መዲና በደማስቆ አቅራቢያ የሚሳኤል ጥቃት ማድረጓ ተገለጸ ፡፡

ጥቃቱ ትኩረቱን ያደረገው የኢራን ወታደራዊ  ኃይል ላይ መሆኑ እንዳልቀረ ተጠቁሟል፡፡

በሶሪያ ደማስቆ አካባቢ የሚገኘውን ወታደራዊ ጣቢያ እስራኤል መምታቷን ተከትሎ እየወጡ ያሉት መረጃዎች ውጥረት የማያጣትን ማዕከላዊ ምስራቅ ሌላ የራስ ምታት ውስጥ እንዳይጥላት እየተሰጋ ይገኛል፡፡

እንደ የሶሪያ መንግስት የዜና አዉታር  ሰንዓ  እና መቀመጫዉን በሀገረ እንግሊዝ ውየሶሪያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ዘገባ የደማስቆሱን ወታደራዊ ጣቢያ እንዳልነበረ ያደረገች እስራኤል መሆኗ እርግጥ ሆኖዋል፡፡

ሁለት መሬት ለመሬት የተለቀቁ የእስራኤል ሚሳኤሎች በሶሪያ የአየር ኃይል እንዲቋረጥ ቢደረግም የወታደራዊ ጣቢያውን ግን ክፉኛ መጉዳቱን የአይን እማኞች ለሶሪያ መንግስት የዜና አዉታር ሰንዓ ተናግረዋል፡፡ በክስተቱ ላይ አስተያየቱን እንዲሰጥ በሲኤን ኤን የተጠየቀዉ የእስራኤል ወታደራዊ ኃይል ግን በሶሪያዉ ጥያቄ ላይ ምንም ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡

ጥቃቱ የተሰነዘረው በእስራኤል እና ሶሪያ መሃከል እያደገ በመጣውን ውጥረት መሆኑ ግን በመዘገብ ላይ ይገኛል፡፡   ባሳለፍነዉ የፈረንጆቹ ወርሃ ህዳር ላይ የእስራኤል ወታደራዊ ሃይል ሶሪያ የ1974ቱን የተኩስ አቁም ስምምነት በመጣስ በሰሜናዊዉ የጎላን ወታደር አልባ ቀጠና ላይ የግንባታ ስራዎችን እያከናወነች ነዉ ስል ወቀሳ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

ቅዳሜ ምሽት በእስራኤል ተከወነ የተባለዉ  የደማስቆሱ የሚሳኤል ጥቃት ከተደረገ በኋላ በሰዓታት ውስጥ ድምጻቸውን ያሰሙት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ኢራን የጦር ሠራዊቷን በሶሪያ ምድር ማሰማራትዋን በማስመልከት ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ልከውላታል፡፡

ቅዳሜ ምሽት በቪዲዮ ተቀናብሮ በወጣዉ የኔትንያሁ መልዕክት የእስራኤልን ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ ስለመስራታቸው መልዕክታቸዉን በተደጋጋሚ አስተላልፈዋል፡፡

እናም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔትንያሁ ሲናገሩ፡ መንግስታዊ አገዛዙ በሚያገኘዉ የኒዉክለር መሳሪያ በዚህም ዘመን የጀዉሽን መንግስት ለማዉደም የሚደረገውን ሴራ አንድም እርምጃ እንዲጓዝ አንፈቅድም ብለዋል፡፡

ይህን መንግስታዊ አገዛዝ በሶሪያ የራሱን ወታደራዊ ሀይል በመገንባት የእስራኤልን መንግስት የማጥፋት አላማውን እስኪያሳካም ፋታ አንሰጠውም ሲሉ ኔታንያሁ የመንግስታቸውን አቋም አስረዱ፡፡ ስለ የደማስቆሱ ጥቃትም ሆኔ የጥቃቱ ትኩረት ግን ምንም የሠጡት ቀጥተኛ ጥቆማ የለም፡፡

እስራኤል በሶሪያ የእርሰ በእርስ ጦርነት ለየትኛዉም ወገን የያለመወገን መርህን ትከተላለች፡፡ ነገር ግን በሶሪያ ምድር በተለይም በድንበሯ አቅራቢያ ይህ የቀይ መስመሬ ነዉ በምትላቸዉ ስፍራዎች ተደጋጋሚ ጥቃቶችን አከናዉናለች፡፡

ይህን የሚታደርገዉ ደግሞ የኢራኑ ሄዝቦላ ወኪል ከሶሪያ መንግስት አገዛዝ ጋር በመሆን በእስራኤል ድንበር አቅራቢያ የወታደራዊ ቀጠና ለማቋቋም የሚያደርገውን ጥረት በጥብቅ ለመከላከል ስለመሆኑ ይወራል፡፡

እናም የአሁኑ የእስራኤል ጥቃት ባሳለፍነው መስከረም ወር ላይ ካደረገችዉ ጥቃት ጋር የሚመሳሰል ተብሎለታል፡፡ በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ የተከናወነዉ ያ ጥቃት በአከባቢዉ ያሉትን ወታደራዊ ቁሳቁሶች ማውደም ቀዳሚ ኢላማው ነበር፡፡

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፊሊስጤም እና ኢስራኤል ለዘመናት የተዋጉባት ኢየሩሳሌም ከተማ የእስራኤል መዲና ናት በሚል ቅዳሜ ዕለት መናገራቸውን ተከትለዉ የተፈጸመዉ ጥቃቱ ከጀርባው ረጅም እጅ ሳይኖርበት እንደማይቀርም እየተዘገበ ይገኛል፡፡

የትራምፕን ንግግር ተከትለው ግን የአረብ ሊግ ሀገራት ቁጣቸዉን በማሰማት ላይ ይገኛሉ፡፡ የአረብ ሊግ ዋና ጸሃፊዉ አህመድ አቡል ጌሄት እንዳሉም ዩ ኤስ አሜሪካ ኢየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማ ማለቷ በቀጠናዉ ፅንፈኝነትና አመፅን የሚቀሰቅስ ነዉ ብለዋል፡፡

ፓሌስታይኖች ኢየሩሳሌምን የወደፊት መንግስታቸዉ መዲና ማድረግን ይሻሉ፡፡ እስራኤል በበኩሏ ከተማዋን የጂዉሽ፣ የሙስሊም እና የክሪስቲያን ቅዱስ ስፍራ ለማድረግ የያዘችዉን ዉጥን የሚቃወሙ የዓለም ዓቀፍ ማህበረሰብ በርካቶች ናቸዉ፡፡  ( ምንጭ: የሲ ኤን ኤን እና አልጀዚራ )