የቀድሞ የየመን ፕሬዚዳንት አብዱላህ ሳላህ ተገደሉ

የቀድሞ የየመን ፕሬዚዳንት አሊ አብዱላህ ሳላህ በትናንትናው ዕለት ተገደሉ  ።

የቀድሞ ፕሬዚዳንት አሊ አብዱላህ ሳላህ  በደጋፊዎቻቸውና በሁቲ  አማጺያን  መካከል  በየመን  ዋና ከተማ ሰንዓ  በተደረገ ጦርነት  መገደላቸውን  ቢቢሲ ዘግቧል  ።   

በአብዱላህ ሳላህ  የሚመራው  የጀነራል ፒፕልስ  ፓርቲ  ኮንግረስ  ፓርቲ ያወጣው  መረጃ  እንደሚያመለክተው  የቀድሞ ፕሬዚዳንት  የተገደሉት  በደቡብ ሰንዓ  በተፈጸመ  ጥቃት መሆኑ   ተገልጿል  ።           

የሃውቲ  አማጺ ቡድን  መሪ  አብዱላህ ሳላህ መገደል  ወሳኝና መልካም  አጋጣሚ  መሆኑን  ተናግረዋል  ።   

አብዱል  ማሊክ  አልሃውቲ በበኩላቸው ለቢቢሲ እንደገለጹት አብዱላህ  ሳላህ በሳውዲ ጥምር  ጦር  ድጋፍ  የበየመን  በተለያዩ  ሃይሎች መካከል የሰላም ስምምነት እንዲደረስ  ጥረት  በማድረግ ላይ  እያሉ  ነው  የተገደሉት  ።   

በየመን  ሰንዓ  ከተማ በሳውዲ ጥምር ጦር አማካኝነት በሰንዓ ከተማ የሚካሄደው የአየር ድብደባ በአጠቃላይ  በየመን የሚካሄደውን ጦርነት  ይበልጥ እንዲስፋፋ  ያደረገው መሆኑን    የተባበሩት  መንግሥታት ድርጅት  ጠቁሟል  ።

በሰንዓ  የሚገኘው የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እንዳመለከተው  በሰንዓ  ከተማ  መንገዶች በታንክና  በብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች  የተሸፈኑ ሲሆን በተባባሩት  መንግሥታት  ድርጅት  ቅጥር ግቢ አቅራቢያ  ከፍተኛ  ውጊያ  መካሄዱ ድርጅቱ  አስታውቋል ።       

 

የዓለም  አቀፉ  ቀይመስቀል እንደገለጸው  ባለፈው አርብ  በየመን ሰንዓ ከተማ  በተቀሰቀሰው   ጦርነት   ቢያንስ  125 ሰዎች መገደላቸው  የተረጋጋጠ  ሲሆን  ከ230 የሚበልጡ  ሰዎች በጦርነቱ  ቆስለዋል ።      

በየመን  የመንግሥታቱ  ድርጅት  የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ጃሚ ማክጎልድሪክ በየመን በጦርነት  ቀጣና አካባቢ የሚገኙ የመናውያን እርዳታ እንዲያገኙ  ጥሪ  ያቀረቡ ሲሆን   ሰብዓዊ  እርዳታ ደርጅት ሠራተኞች  የሰው ህይወትን ለማዳን የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ማሳሰቢያ ሠጥተዋል  ።