በ2018 ከፍተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ በዓለም እንደሚከሰት ተመራማሪዎች አስጠነቀቁ

የአሜሪካ ተመራማሪዎች በ2018 ከፍተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ሊከሰት እንደሚችል ተመራማሪዎች አስጠነቀቁ ፡፡                   

አላማችንን እያሳሰባት ያለው በተፈጥሮ ምክንያት የሚከሰቱ አደጋዎች መሆናቸውን ብዙዎቻችን እያስተዋልነው ያለ ጉዳይ ነው እነዚህ አደጋዎች ደግሞ  ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበዙ መጥተዋል ከነዚህ የተፈጥሮ አደጋዎች መካከል ደግሞ የመሬት መንቀጥቀጥ አንዱ ነው፡፡

ታዲያ ይህ የተፈጥሮ አደጋ ያሳሰባቸዉ ተመራማሪዎች በጉዳዩ ዙሪያ ምርምር  አድርገዋል፡፡  በመርምራቸውም እኤአ በ2018  ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ከዚህ ቀደም ከነበሩት የከፋ ሊባል የሚችል የመሬት መንቀጥቀጥ በአለማችን ላይ ተጋርጦባታል  ብለዋል፡፡

ታዲያ ይህ አደጋ በአለማችን ዙሪያ የሚከሰት ሲሆን በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ርዕደ መሬቱ ከፍተኛ እንደሚሆን ባደረጉት ምርምር ማረጋገጣቸውን የኮሎራዶና የሞንታና ዩኒቨርሲቲ  የሆኑት ሮበርት ቢልሃም  እና  ርብቃ ቤንዲክ ምርምራቸውን በአሜሪካ የጂኦሎጂ ማህበረሰብ ኮንፍረንስ ባቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

የመሬት የሽክርክሪት ፍጥነት እና በዓለም አቀፋዊ የመሬት መንቀጥቀጥ እንቅስቃሴ መካከል ቀጥተኛ ተዛምዶ መኖሩን በምርምራቸው አረጋግጠዋል፡፡

በተፈጠሩ አምስት አጋጣሚዎች  ውስጥ የርዕደ መሬት መጠኑ ወይም ሬክተር ስኬል በየዓመቱ ከ25 እስከ 30 በመቶ እየጨመረ  እንደሄደና ከ7 ነጥብ 0 እና ከዚያ በላይ እየተመዘገበ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

የመሬት ሽክርከሪት መጠነ ፍጥነት ብዙ ጊዜ የማይዛባ ሲሆን  የቀናትን ርዝማኔ በማይክሮ ሰከንዶች እንደሚለወጥ በጥናታቸዉ አመልክተዋል፡፡ ይህ ቢሆንም ግን  ሽርፍራፊ ሰከንዶች ተደምረው የሚያስገኙትና በየቀኑ  የሚጨመሩ ደቂቃዎች የመሬትን የውስጥ ኃይል በመጨመር የመሬት መንቀጥቀጥ እንዲከሰት ያደርጉታል  ብለዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ የመሬት መንቀጥቀጡ ወደፊት ሊከሰቱባቸው የሚችሉ ሀገሮችና ቦታዎች በግልጽ ለያስቀምጡ ባይችሉም  በምድር ወገብ እና በደቡብ ምስራቅ እስያ ጠንካራ የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እንደሚደርስ ግን ይታወቃል፡፡ ( ምንጭ: ሲጂቲኤን)