በኢንዶኔዥያ በባሊ ተራራ የተከሰተው እሳተ ገሞራ ፍናዳታ ከፍተዓ ስጋት ፈጥሯል

በኢንዶኔዥያ ባሊ ተራራ የተከሰተው ተብሎ የእሳተ ገሞራ  ፍናዳታ እጅግ ከፍተኛ  ደረጃ ያለው ሊሆን እንደሚችልተሰግቷል፡፡

እሳተ ገሞራው ይከሰትበታል ከተባለው የባሊ ተራራ ዙሪያ የሚገኙ ነዋሪዎችን ለማስነሳት ሀገራት ደፋ ቀና እያሉ ነው፡፡

የኢንዶኔዥያ ባለስልጣናት እንደገለጹት እሳተ ገሞራው ከፍተኛ ደረጃ ያለው ነው፡፡

በዚሁ የስጋት ቀጣና አካባቢ የሚገኘውና ከፍተኛ የቱሪስት እንቅስቃሴ የሚያስተናግደው የአይስላንድ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት ተዘግቷል፡፡

እንደ ባለስልጣናቱ ገለጻ ከሆነ ጥቁር ጭስ እና አመድ ከተራራው በላይ እስከ 3 ሺህ 4 መቶ ሜትር ከፍታ በመታየት ላይ ላይ ሲሆን አልፎ አልፎ እሳትም ይታያል ፡፡

በተራራው አቅራቢያ የሚገኙ ሰዎችም ከተራራው አናት ከሚወርዱ ድንጋዮችና ፍርስራሾች በመራቅ ከአደጋው ራሳቸውን እንዲከላከሉም ባለስልጣናቱ አስጠንቅቀዋል፡፡

እንደ ብሄራዊ የአደጋ መከላከል ቦርድ ገለጻ የእሳተ ገሞራው ደረጃ አራት የሚባለው ሲሆን አደጋው የመከሰት እድሉም ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡

እሳተ ገሞራው በተለያዩ ፍንዳታዎች እና የእሳት ነበልባሎች የሚታጀብ ሲሆን ፍንዳታው እስከ 12  ኪሎ ሜትር ድረስ ይሰማል ነው የተባለው፡፡

ከተራራው አናት ላይ የሚፈነጥቀው የእሳት ጨረር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑ በምሽት ላይ በግልጽ የሚታይ ሲሆን ይህም የፍንዳታው መጠን ከፍተኝነትን ያሳያል፡፡

የአየር መንገዱ ባለስልጣናት እንደገለጹት 445 በረራዎች የተሰረዙ ሲሆን ከ59 ሺህ በላይ መንገደኞች ከጉዟቸው ተስተጓጉለዋል፡፡(ቢቢሲ)