በ2018 ብቻ 2 ሺ 200 ስደተኞች በሜድትራንያን ባህር ሞተዋል

 

በፈረንጆች 2018 ዓመት ብቻ 2 ሺ 200 ስደተኞች በሜድትራንያን ባህር መሞታቸውን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ በዚህ የፈረንጆች ዓመት 113 ሺ ያልተመዘገቡ ስደተኞች ወደ አውሮፓ አገራት መግባታቸውንም ነው የገለጸው፡፡

እንደ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ሪፖርት ወደ አውሮፓ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር ከባለፈው ዓመት ሲነፃፀር በ59 ሺ የቀነሰ ቢሆን የሟቾች ቁጥር ግን አሁንም ከፍተኛ ነው፡፡

በዚህ ዓመት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሞቱት 4 ሺ 503 ስደተኞች የሜድትራንያን ባህር የ2 ሺ 200 ስደተኞች ህይወት በመቅጠፍ 50 ከመቶ ድርሻ ይዟል፡፡

ያለፈው ሰኔ ወርም የ629 ስደተኞች ህይወት ያለፈበትና ከፍተኛ የሞት ቁጥር የስተናገደበተ ወር ሆኖ ነው የተመዘገበው ፡፡(ምንጭ፡ፕረንሳ ላቲና)