በትግራይ ክልል በተለያዩ ከተሞች የ4ጂ ኔትወርክ አገልግሎት ተጀመረ

የኢትዮ-ቴሌኮም የሰሜን ክልል አስተባባሪ ሙሉ ወልደስላሴ

ሕዳር 14/2016 (አዲስ ዋልታ) በትግራይ ክልል በተለያዩ ከተሞች የ4ጂ ኔትወርክ አገልግሎት መጀመሩ ተገለጸ፡፡

የኢትዮ-ቴሌኮም የሰሜን ክልል አስተባባሪ ሙሉ ወልደስላሴ የ4ጂ የኔትወርክ አገልግሎት ከተጀመረባቸው የትግራይ ከተሞች መካከል መቐለ፣ አዲግራት፣ አድዋ፣ አክሱም፣ ሽሬ እና ውቅሮ ከተሞች ይገኙበታል ብለዋል፡፡

የ2ጂ እና 3ጂ ሲም ካርዶች ተጠቃሚዎች ወደ ቴሌኮም ማዕከላት በመሄድ ወደ 4ጂ ሲም ካርዶች በነፃ መቀየር እንደሚችሉም ኃላፊው መግለፃቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡