ኢትዮጵያዊ የእርቅ ስርአት ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

የካቲት 18 /2013 (ዋልታ) – የሰላም ሚኒስቴር “የሰላም ወግ” በሚል ርዕስ ባዘጋጀዉ የውይይት መድረክ “ኢትዮጵያዊ እርቅ ምንድን ነው?” በሚል መርህ ኢትዮጵያዊ የእርቅ ስርአት ከሃይማኖት፣ ከባህል፣ ከፍልስፍና አንፃር ያለዉን ጠንካራ ጎን በሚመለከት ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

አለመግባባቶችና ግጭቶች በሀገራዊ የሽምግልና፣ የእርቅ ስርአት እና የግጭት አፈታትን በመጠቀም የሚፈጠሩ ግጭቶችን ማስቀረትና ሰላምን ማፅናት ስለሚቻል ኢትዮጵያዊ የእርቅ ስርአት ላይ ሊሰራ እንደሚገባ በመድረኩ ተነስቷል።

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬ አለም ሽባባዉ እርቅ በአንድ ሀገር የዴሞክራሲ ግንባታ ላይ ያለዉ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ያሉብንን ችግሮችና አለመግባባቶች ኢትዮጵያዊ በሆነ ዘዴ በመፍታትና እርቅ በማውረድ ሰላምን ማስቀደም እንደሚገባ ተናግረዋል።

(በሕይወት አክሊሉ)