ኮሚሽኑ አጀንዳዎችን በማሰባሰብ ሂደት የሚሳተፉ ባለድርሻ አካላት መለየቱን አስታወቀ

ሐምሌ 21/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለሚያከናውነው አጀንዳዎችን ለማሰባሰብ ስራ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት መለየቱን አስታወቀ፡፡

ባለድርሻ አካላትም በኮሚሽኑ በሚቀርብላቸው ጥሪ መሰረት በሚደረገው አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተጠይቋል፡፡

የተለዩት ባለድርሻ አካላትም በየወረዳው ከሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የተመረጡ ተወካዮች፣ መምህራን ማህበር፣ ሲቪል ማህበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የአሰሪዎች ማህበራት እና የሰራተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን መሆናቸው ተመላክቷል፡፡