የዓለም ባንክ ለአፍሪካ የኮቪድ-19 መከላከያ የክትባት ግዢ 12 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ሊያደረግ ነው

የዓለም ባንክ ለአፍሪካ ኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት መግዣ የሚሆን 12 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ብድር ሊሰጥ መሆኑን አስታውቋል።

የኮሮና ወረርሽኝንና መከላከያ ክትባቱን አስመልክቶ በቨርቹዋል በተደረገ ውይይት የዓለም ባንክ የአስቸኳይ ጊዜ የኮቪድ-19 መከላከያ የፋይናንስ ድጋፍ ለተመረጡ የአፍሪካ አገሮች እንደሚሰጥ ይፋ አድርጓል።

በዚህም ኢትዮጵያን ጨምሮ ጋና፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኒጀር፣ ሞዛምቢክ፣ ቱንዚያ፣ ኢስዋቲኒና ኬፕ ቨርዴ የድጋፉ ተጠቃሚዎች መሆናቸውን ዩሮ ኤዤይ ሪቪው አስነብቧል።

ባንኩ ያደረገው ድጋፍ በረጅም ጊዜ ሚከፈል ብድር መሆኑም ነው የተገለጸው።

የአለም ባንክ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ የአፍሪካ አገሮችን ኢኮኖሚና የጤና ሴክተር ለመደገፍ 25 ቢሊዮን ዶላር ብድርና እርዳታ የሰጠ ሲሆን እስከ መጪው ሐምሌ ድረስ ደግሞ ተጨማሪ 15 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርግ መነገሩን ኢዜአ ዘግቧል።